Free songs
Home / Mark's Corner / Mark’s Corner 6: አብሮ መሥራት…በጋራ መበልጸግ

Mark’s Corner 6: አብሮ መሥራት…በጋራ መበልጸግ

Mekuria-M-Negia

Mekuria M. Negia

አብሮ መሥራት…በጋራ መበልጸግ

የዛሬውን መልዕክት እና ምክር በሀገራችን በኢትዮጵያ ለዘመናት በሚነገር ምሳላዊ አባባል ልጀምር «አንድ እጅ አያጨበጭብም…አንድ ሰው እፈርድም» በሚለው። ይኽ ታላቅ ቁምነገርን ጠቅልሎ የያዘ አባባል የሚነግረን በነጠላ ከሚደረግ ተግባር ይልቅ በቡድን ወይም በጋራና በኅብረት መሥራት ያለውን ጠቃሚነት  የሚገልፅ ነው።

በእርግጥም በግል አንድ ብቻ ሆኖ በተናጠል ለማደግ የሚቻልና ይኽም በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ የተለመደ ቢሆንም ቶሎ ውጤቱን ወይም አትራፊነቱን ለማየት አስቸጋሪ እንደሆነ በሥራዬ ጠባይ ለማረጋገጥ ዕድሉን አግኝቻለሁ።  በጋራ መሥራት በመልመድ እውቀትን፣ ገንዘብን፣ በተለይ ንግዱን ከመጀመር በፊት ለሥራው የሚያስፈልጉ የተለያዩ መረጃወዎችን ከሁሉም አቅጣጫ አሰባስቦ ጠንክሮ እና ተማክሮ በመስራት ለውጤት በማብቃት አብሮ ማደግ ይቻላል።

ብዙዎች «ኢትዮጵያን አብሮ መብላት እንጂ አብሮ መሥራት አይችሉም» የሚል የተሳሳተና አንድነታችንን በሚያራርቅ አባባል ኅብረታችንን ለማኮላሸትና ለማቃለል ሲሞክሩ እናያለን። አባባሉና የመጥፎ ምሳሌ ምልክት መሆኑ ግን ከእውነት የራቀ በእኛ በኢትዮጵያውን ላይ ፍፁም  የማይታይ «ጠላት ፈጠር» አባባል ሲሆን በኢትዮጵያውያን መሐል ማኅበራዊ ሕይወት ከጥንት ጀምሮ የዳበረ መሆኑን ለማስመስከር «እድር፣ እቁብ፣ ደቦ…» የመሳሰሉት በቂ ምስክሮች ናቸው።

ባሁኑ ወቅት በኅብረት ከአነስተኛ የንግድ ዓይነት ወደ ከፍተኛው ለመሸጋገር ያልደፈርነው «ፍርሃት» የተባለውን ማነቆ መስበር ስላቃተን እንጂ ለመተባበር እኛን የሚያክል ሕዝብ አይኖርም። ብዙ ጊዜ ስለሌሎች ዜጎች በተለይም ስለ እስራኤል፣ ኮሪያ እና የመሳሰሉት ዜጎች መጠቃቀምና ተማምኖ መስራትን እንደምሳሌ ስናወሳ እመንሰማለን። እነዚህ ሰዎች ያደጉትና አብዛኛውን ቢዝነስ ለመቆጣጠር የቻሉት እንዴት ነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ብንሞክር ግን መልሱ «በጋራ፣ በመተባበር እና በመተማመን መሥራት» ከመሆን አይዘልም። እኛስ በከፍተኛ የንግድ ዘርፍ ላይ በጋራ ተሳትፎ ለማድረግ ምን የሚያቅተን አለ?

ኢትዮጵያውያንን ከአነስተኛ የግል ንግድ ይልቅ ወደ ከፍተኛ እና በአክሲዮን በተሳሰረ ዘርፍ ለማሳተፍ በቅርቡ እኔው ራሴ ሙሉ ተሳታፊ የሆንኩበት «ኢትዮራን» “ETHIORUN LLC” የተሰኘ ተቋም መስርተናል። ይኽ ተቋም ዋናው ዓለማው ኢትዮጵያውያንን ከፍተኛ በሆነ የቢዝነስ መስክ ከፍተው አትራፊ እና የከፍተኛ ካፒታል ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል ነው። በጋራ መሥራት ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ በለንደን ኦሎምፒክ ላይ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውጤቱን አይተናል። በጋራ ደክሞ ውጤታማ መሆን!

በዚህ “ETHIORUN LLC” በተባለው አክሲዮን ማኅበር ውስጥ ለመሳተፍ የሚያስፈልገው ቀና አመለካከት፣ በልምድ የተገኘ ዕውቀት፣ በአቅም ላይ የተመሰረተ ገንዘብ እና ጠንክሮ ለመሥራት ቃል መግባት ብቻ ነው። ይኽን አክሲዮን ማኅበር በጥቂት እርስ በርስ በሚግባቡ፣ በሚተማመኑ፣ በዓላማው ባመኑ እና በጋራ ለማደግ ፍቃደኛ በሆኑ ሰዎች ቀስ በቀስ የሚያድግ ይሆናል።

በእርግጥ በኅብረት መሥራት ያስፈልጋል ስንል፣ በጋራ ምን ዓይነት የንግድ  ሥራ መስራት ይቻላል? ብለው ለሚጠይቁ ሰዎች መልስ መስጠት ተገቢ ይመስለኛል።

ገንዘባችንን፣ በተለያየ ግዜና ቦታ ያጠራቀምነውን ዕውቀትና የሥራ ልምድ ማስተሳሰርና በኮሚኒቲያችንም ያልተሟላውን ወይም ያልተሞከረውን የአገልግሎት ዘርፍ አጥንቶ የሚዘረጋ የጋራ ድርጅት መፍጠር ነው።

ይኽንንም በተግባር የሚተረጉመው “ETHIORUN LLC አክሲዮን ማኅበር የዚህ ፅሑፍ አቅራቢ ሙሉ በሙሉ የምሳተፍበት ከማርክ ኮምፒውቲንግ እና የሂሳብ አያያዝ ቢሮ ጋር በመተባበር ይኽንን የአክሲዮን ማኅበር ለውጤት ለማብቃት በትጋት እየሰራን እንገኛለን። በዚህ ጉዳይ ላይ በቂ እና የተሟላ ዕውቅና ለማግኘት  ወደ እኛ በመምጣት ሙሉ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ። ይኽን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን በቅርብ የምትተዋወቁ እና በመተማመን እንዲሁም ሕጋዊ የሆነ አክሲዮን አቋቁሞ ለመሥራት ፍላጎቱ ያላችሁ ማንኛውንም ነፃ የሆነ ሙያዊ ምክር ለመስጠት ዝግጁ ነን።

በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ የንግድ ሥራ ሲታሰብ ብዙዎቻችን ትናንሽ ሱቅ ወይም ምግብ ቤት እና  የመሳሰለው  ላይ ብቻ የማተኮር አዝማማሚያ በሰፊው ይታያል። ለምን? በዚህ ብቻ ተወሰንን? ብለን ራሳችንን ብንጠይቅ ግን ከውስጣችን ያጣነው «ድፍረትን ማጣት እና ፍርሃትን ማስወገድ» ሆኖ እናገኘዋለን።  ባለንበት ሀገር ሕግ መሠረት በሠነድ አስደግፈን የተሻለ ትርፋማ የንግድ ዓይነት፣ ለምሳሌ የገበያ ማዕከል (MALL) እና አፓርትመንት በንብረትነት ገዝቶ በማስተዳደር መያዝ፣ የኢንሹራንስ ካምፓኒ፣ ባንክ፣ ትራንስፖርቴሽን ካምፓኒ እና የመሳሰሉትን ጥናት በማድረግ ሥራችንን ሳንተው ገቢያችንን ይዘን ይኽን በጎን በማደራጀት በቡድን በአንዱ የተያዘውን ኮፒ በማድረግ ሳይሆን ለየት ያለና የተሻለውን የሥራ ዓይነት ላይ ገንዘብ እና እውቀታችንን አስተባብረን እንደግበት።

ከላይ ያነሳሁት “ETHIORUN LLC” «ኢትዮራን አክሲዮን ማኅበር» በንግድ ዘርፉ የመጀመሪያው ዕቅድ እና ግብ የገበያ ማዕከልና አፓርትመንት መግዛት እና ማስተዳደር ነው።

ይኽን ጽሑፍ ለምታነቡ እና  ፍላጎቱ ያላችሁ ወገኖች ሁሉ  የወደፊት ተጠቃሚ ለመሆን መረጃዎችን በስልክ በመጠየቅ ወይም ቢሮአችን ድረስ በመምጣት በቅርብ ብታናግሩን ሁሉንም በግልፅ እና በዝርዝር በመረዳት ውሳኔ ላይ መድረስ ትችላላችሁ። በእኛም በኩል ዝርዝር ጥናቱን እና በጋራ የሚቋቋመው አክሲዮን ማኅበር ሊያስገኝ የሚችለውን በማስተማር፣ ጥናቱንም በማሳየት ለውሳኔያችሁ መረጃ ለመስጠት ዝግጁ ነን።

– Mekuria M. Negia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <strike> <strong>

Scroll To Top