Free songs
Home / Editorials

Editorials

  • Editorial 1
  • Editorial 2
  • Editorial 3
  • Editorial 4
  • Editorial 5
  • Editorial 6
  • Editorial 7
  • Editorial 8
  • Editorial 9
  • Editorial 10

አስደንጋጭ ሃሳቦች

በፊት የማውቀውን የ‹‹ቃለ ምሕረትን›› ትርጉም ፍለጋ መዝገበ ቃላት ማገላበጥ ገባሁ፡፡ ባልሳሳት ከሦስት በላይ የአማርኛውን የቃል ፍቺ ሰጪዎች መጻሕፍት ጎብኝቻለሁ፡፡ እንዲያው ለነገሩ እንጂ ይኽ በየዕለቱ ከአፋችን በተለያዩ ሌሎች ቃላቶች ታጅቦ የሚወጣው አንድ ፈርጅ ቃል ‹‹ምሕረት›› አዲስ ሆኖብኝ አይደለም፡፡ ዛሬ ለምለው ወይም ልዘምትበት ለተነሳሁበት ጉዳይ ሁለት ፍቺ ኖሮት ችግር ውስጥ እንዳይከተኝ ለመጠንቀቅ ስል ነው፡፡ የቃሉ ሙሉ ትርጉም በየመዝገበ ቃላቱ እንዲህ ይነበባል፡፡

ምሕረት፡- ማረ፣ ይቅር አለ፣ ያለፈውን በደል ሻረ፣ ለተበደለው ይቅርታ አደረገ፡፡ ይላል መፅሐፉ፡፡

የእኔ አነሳስ ግን ይህንን ትርጉም መሠረት በማድረግ፣ የሰው ልጅ ከዓመተ ዓለም ወደ ዓመተ ምሕረት ከተሸጋገረ በኋላ ነው ወይስ በፊት መከራና ፍዳ የበዛበት? በእርግጥ ዓመተ ምሕረት የተሰኘው የምሕረት ዘመን ቃልና ትርጉሙን ጠብቋል ወይ? ከሚለው በመነሳት ላይ የመነጨ ነው፡፡

በቃል ኪዳን ቃሉ ፈጣሪ ‹‹ከሠማያት ሠማያት ወርጄ ከድንግል ማሪያም ተወልጄ›› በሚለው ቃሉ የሰውን ልጅ ኃጢያት አንፅቶ ያለፈውን በደል ሽሮ ከጥፋት ሊድነው ወደዚህች ዓለም ሲመጣ፣ ተስፈኛው የሰው ልጅ ቃሉን የወሰደው በጥሬው በመሆኑ የፈጣሪን ቃል እና ትዕዛዛት ባለማክበሩ እንደገና ወደ ጥፋት ተመልሶ ያለፈ እና የተሻረለትን ጥፋቱን በእጥፉ ሳይተካው ይቀራል? (…Continued)

Read Full Editorial

አድሕሮት ወይስ አምልኮት!

ድሮ ሕፃን እያለን በጨቅላ አእምሮ ትንሹ ነገር ሁሉ ያስቀን ነበር። የአበው ቀልዶች ደግሞ ለሕፃናት የሲኒማ ያህል በሳቅ የማንፈራፈር ኃይል ነበራቸው። ያኔ ሕፃን ሆነን።

 የሌላውን ባላውቅም ትዝ የሚለኝ በልጅነት ጊዜዬ ቀላል ቀልዶች እንደዚያ ያስቁኝ ነበር። አሁን በጎልማሳ ዘመናችን ግን ከቴክኖሎጂው ጋር ቀልዱም ሆነ ዘፈኑም ተቀይሮ እና በአዲስ ዘመን አመጣሽ ስታይል ታጅቦ ካልቀረበ፣ እንኳን ሊያስቀን ቀርቶ ፈገግም አያሰኘን። ያውም የመድረክ አስቂኙ እንደ አሸን በፈላበት እና የቀልዱም የማሳሳቅ ኃይሉ በፉክክር አድጎ ለየትኛው ቀልድ እንደምንስቅም ግራ በተጋባንበት ዘመን።

 ልጅነት ጥሩ የየዋሕነት ጊዜ ነው። በአጋጣሚ በሠፈራችን የሚያልፍ ነጭ ሰው ስናይ፣ ዐረብ ይሁን ቻይና፣ ሜክሲኮያዊ እንግሊዛዊ እየተከተልን «ፈረንጅ፣ ፈረንጅ» እያልን እርምጃችንን ከእርምጃው ፈጠን እያደረግን እንከተለው ነበር። በፀጉረ ልውጥነቱ፣ በፊቱ ንጣት በፀጉሩ ዘንፋላነት። አይ ልጅነት ሞኙ! ያ ፀጉረ ልውጥ በሃገሩ በረንዳ አዳሪ ይሁን፣ ደሃ ይሁን ኃብታም የምናውቀው ነገር የለም። ነጭ በመሆኑ መከተል፣ ማድነቅ ካሰኘንም እንዘፍንለታለን። ደግሞ የከረሜላ መግዣ እንለምነዋለን። ወይ ይሰጠናል፣ አሊያም በሃገሩ ያላገኘውን አጀብ እየኮራበት ሠፈራችን ደጋግሞ ብቅ ይላል። ይኽን ያለምክንያት አላልኩትም። ጅምሬ ለምለው ነገር በር ሊከፍት ይችል ይሆናል ብዬ አስባለሁ። በድሮ ነገር ጀምሬያለሁና በዱሮ ቀልድ፣ ያኔ ያስቀን በነበረው ወደ ቁምነገሬ ልግባ። (…Continued)

Read Full Editorial

ወቀሳ እና ትውልድ

እንደዚህ ዓይነት መልእክት ወይም ተመሳሳዩን ሳስተላልፍ የመጀመሪያዬ አይመስለኝም፣ መልኩ ይቀያየር እንጂ መስመሩ ከአንድ መንገድ የወጣ አይደለም። ለዚህም ብዙ ምክንያቶች አሉኝ።

 አንድ ሠሞን ለምን የፖለቲካ ድርጅቶች ሌላውን ከመንቀፍ እና መንግሥት ከተቃዋሚዎች ጋር የዕርቅ በሩን ለድርድር እንዲከፍት መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ለምን እርስ በእርሳቸው ተቃዋሚዎች አይታረቁም ወይም በስምምነት አንድ አይሆኑም የሚል የቅሬታ ፅሑፍም ለንባብ ያበቃሁ መሰለኝ።

 በሃገራችን ውስጥና በውጪው ዓለም ከ1966 እ.ኢ.አ. የተቋቋሙ የፖለቲካ ድርጅቶች በቁጥር ከአንድ መቶ ዘለል ብለዋል። ይኽ ቁጥር በአንድ ወቅት እንደ ጤዛ ታይተው የጠፉትን እና ለአንድ ዒላማ ለአንድ ወሳኝ ወቅት የተቋቋሙትንም ይጨምራል። እንግዲህ ይታያችሁ አሜሪካንን ለሚያክልና ቁጥሩ ከ360 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ለሚኖርባት ሀገር የፓርቲዎች ቁጥር ከሁለቱ አንኳር ፓርቲዎች ጋር ተደምረው 4 ብቻ ናቸው። እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምረጡኝ ቅስቀሳ ጀምሮ የሕዝብ ተቀባይነት እና ውክልናቸውን ካገኙበት ቀን በተሰጣቸው ወንበር ላይ ሆነው የመረጣቸውን ሕዝብ ለማገልገል ይጥራሉ። በሥራ ዘመናቸው ሲያጠፉ እና ሕዝብን ሲያስቀይሙ ይሻራሉ፣ ወይም በሕጉ መሰረት ቅጣት ይፈፀምባቸዋል። ከጉባኤ አባል፣ ሴኔተር፣ ሃገረ ገዢ የሚባሉ ሁሉ በሥራ ዘመናቸው ላጠፉት ጥፋት ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ቅጣታቸውን ወደሚያገኙበት ወሕኒ ለመላካቸው በዓይን እማኝነት በማስረጃ ያየነው ነው። (…Continued)

Read Full Editorial

«ሁሉም ወደተዘጋጀላቸው ባዶ ቅርጫት እየዘለሉ ይገባሉ»

የደጉ ጊዜ የምንለው ጠፋ እንጂ፣ እንደ ዛሬው ሳይሆን የሃገሬ ሰው የሚጠራው በስሙ ወይም በሃገሩ ነበር። የሃገር ስም የወል ሥም ነበራ የዛን ጊዜ። ከሃገሩ ከወጣ «ኢትዮጵያዊ»፣ በሃገሩ ደግሞ «እገሌ» ተብሎ በስሙ ይጠራ ነበር። ዛሬ ሁሉ ነገር ተቀያይሯል። ሕዝባችን፣ መሬታችን፣ ከብቶቻችን፣ የታሪክ ቦታዎቻችን፣ ወንዝና ተራሮቻችን፣ ያለፉት አባትና አያቶቻችን ሁሉ ዘር አላቸው። መጠሪያቸው ሃገራቸው እና የትውልድ ስማቸው ሳይሆን የዘር ግንዳቸው ነው።

 ለመሆኑ ዘር ምንድነው? ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? በእርግጥስ ምንድነው? የምንጠራበት ስም የወጣበት ቋንቋ፣ የምንናገረው ቋንቋ፣ መንግሥት የነገረን፣ የትውልድ ቦታችን፣ ያደግንበት ቀዬ? በእርግጥ ለእኛነታችን ማንነት ማረጋገጫው የትኛው ነው? በኦሮምኛ ቋንቋ ስም የወጣለት ሰው ኦሮሞነቱን የሚያረጋግጠው በስሙ ነው ወይስ በተወለደበት ሌላ ግዛት?

 አሁን መንግሥት የሆነው ክፍል በትረ ሥልጣኑን እንደያዘ ሰሞን በአብዛኛው ጊዜው የተጠመደው የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘር እና በክልል ማደራጀት ነበር። በእርግጥም አደረጃጀቱ ሰምሮለታል። ከስምረትም አልፎ እያንዳንዱ ኅብረተሰብ ወደደም ጠላም የመንግሥት ፖሊሲ እና በሕገመንግሥትም ፀደቀ በመሆኑ አምኖ እንዲቀበለው አድርጓል። እነሆ ከሃያ አንድ ረዥም ዓመታት በኋላ «ዘር» የሁሉም ብሔራዊ መዝሙር ለመሆን በቃ።

 ምን መብቃት ብቻ ተቃዋሚ እና ኢትዮጵያን በኢትዮጵያዊነቷ የሚያምኑ ሁሉ የበኩላቸውን ድጋፍ እየሰጡ ነው። እስቲ ከውጪ የዜና አውታሮች እንጀምር፦ (…Continued)

Read Full Editorial

ዓመተ ምሕረት ወይስ ዓመተ ፍዳ?

መጀመሪያ ዓብዮት የሚባል አዲስ ግኝት በደሃዋ አገራችን እንደ ዝናብ ጎረፈ። እኛም በዕልልታ ተቀበልነው፣ በዓብዮቱ የተጎዱም ኃዘናቸው በረታ። 17 የቁጣ እና የሰመመን ዓመታት አስቆጠርን እና ደግሞ ራሳቸውን ነፃ ሊያወጡ ጫካ የገቡት በለስ ቀናቸውና በድንገት እኛንም ነፃ አወጣናችሁ አሉን። ከማን እንደሆነ ባናውቅም ነፃ ወጣን። ነፃ አውጪው በዛና አገራችን በድንገት ነፃ አውጪ በነፃ አውጪ ተጥለቀለቀች።

  ነፃ አወጣናችሁ ያሉን ለሌሎችም ነፃ አውጪ ፈጠሩላቸው። ማ ማንን ነፃ እንዳወጣ ሳናውቅ ሁላችንም ለነፃ አውጪዎቻችን አጨበጨብንላቸው። በጫካ ጥናት የተቋቋሙ ነፃ አውጪዎች፣ በድንገት የተፈጠሩ ነፃ አውጪዎች፣ የሠፈር እና ጎሣ ነፃ አውጪዎች እንደ አሸን ፈሉብን። መለያቸው እንዲሆንም ሁሉም ባለባንዲራ ሆነው የሃገራችንን ታሪካዊውን እና በዱር በገደል ከጠላት ጋር ሲዋደቁ የሞቱለትን ባንዲራ እንደ ጠላት ተቆጠረ።

  ከትናንት ወዲያ ዓብዮት፣ ትናንት ነፃ አውጪ እና የጎሣ ዓብዮት፣ ዛሬስ ምን ታዘብን? ምን ሸተተን? ምን ተዘጋጅቶልናል? በ21ኛው ክፍለ ዘመን በዓለም ብቸኛዋ በዘር ለተደራጀችዋ ሃገር የሚጠብቃት ምን ይሆን? እንግዲህ እዚህ ላይ ነው እነ ጁሐር መሐመድ ብቅ ለማለት አጋጣሚውን የተጠቀሙት።

  የአክራሪ እስልምና ኃይማኖት በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሌሎችም የዓለም ክፍሎች እንዲሁም በሠሜኑ የአፍሪካ ክፍል በአስደንጋጭ እና አሳሳቢ ሁኔታ በተከሰተበት በአሁኑ ወቅት የእነ ጁሐር መሀመድ ግልፅ መልዕክት ያለምክንያት አልነበረም። (…Continued)

Read Full Editorial

የማይታየው ባዶ ቅርጫት

አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳለሁ የልጅ ጠባይ የሌለው እና አንድ ክፍል ውስጥ ለ2 ተከታታይ ዓመታት የነበርን አንድ ተማሪ አውቃለሁ። የታዳጊ ወጣት ጠባይ አይታይበትም። ሁሌ ኮስታራ ነው። ጓደኛ አይፈልግም፣ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ለመግባባት እና ለመጫወት እንኳን ፍላጎት የለውም። ሌሎች ተማሪዎች ስለ እሱ በጣም ቅር ይለናል። በዕድሜ ከእኛ ባይበልጥም በጠባዩ እንሸሸዋለን። እሱም ደንታ የለውም። በእረፍት ሰዓት ከሌሎች ተማሪዎች ፈንጠር ብሎ ራሱን ገለልተኛ ማድረግ ይፈልጋል። በመማሪያ ክፍል ውስጥ እንኳን ከጎኑ የተቀመጠውን ተማሪ አያናግርም። ጋግርታም ብጤ ነው። ታዲያ ይኽ ልጅ ጠባዩ ከማስገረምም አልፎ ያስደነግጠኝ ነበር። ደፍሬ ላናግረው እፈልግና ፈርቼ የተውኩበት ጊዜ ጥቂት አልነበረም። ተፈጥሮ ሆኖብኝ ሰዎችን መስበር እችላለሁ፣ በእሱ ላይ ግን አልተሳካልኝም።

በአንዱ የትምህርት ሴሚስተር አጋጣሚ ይሆንና ጎን ለጎን የመቀመጥ ዕድል ይገጥመኛል። የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሣምንታት ያለምንም ንግግር አለፉ። በአንዱ ሣምንት ላይ ግን የግብረገብ አስተማሪያችን የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ከጎኑ ከሚቀመጠው ተማሪ ጋር የቡድን ሥራ ሠርተን እንድናቀርብ ያዝዙናል። የተሰጠን የቡድን ሥራ ከጊዜ እርዝመት ሙሉው መንፈስ ይዘንጋኝ እንጂ መሠረታዊው ሃሳቡ «ተቃራኒ ነገሮች እንዴት ይስማማሉ?» የሚል ዓይነት እንደነበር ትዝ ይለኛል። የግድ ይሆንና ለሥራው ስንል ከዚህ ልጅ ጋር መነጋገር እንጀምራለን። ሀሳቡን ተከፋፍለን የሚመስለንን አስተያየት በግል ሰርተን እንድናመጣ እና የሰራነውን እንድናስተያይ ከሱው ሃሳብ ይቀርባል። ከተፈጥሮ ባሕርዩ ከእኔ ጋር ቁጭ ብሎ ሃሳብ በማፍለቅ ለመሥራት ፍቃደኛ ካለመሆን የመነጨ እንደሆነ ገብቶኛል። ሃሳቡን (…Continued)

Read Full Editorial

የሐሰት ወሬ አፍላቂና አቀባይ

የሰው ልጅ እንደተፈጥሮው እና እንደ ልምዱ አንድን ነገር የመቀበል ባሕሪዩም ይለያያል። አንዳንዱ ከሰው የሰማውን ነገር ለሌላ ሰው ከመንገሩ በፊት የነገሩን ትክክለኛነት ማጣራት ሲፈልግ፣ ከፊሉ ደግሞ የሰማውን ነገር ሳይጨምርና ሳይቀንስ ለሌላው ማውራት ይወዳል። ከዚህ ባለፈ ደግሞ የሰማውን ነገር ቆርጦ እና ቀጥሎ ለእሱ በሚያመቸው መንገድ ላገኘው ሁሉ የሚያቀብል አለ። ቆርጦ ቀጥል የሚሉት ዓይነት።

 ለምን ይሆን ሰዎች ከማየት ይልቅ መስማት የሚቀናቸው? ለማንበብ ወይም በቦታው ከመገኘት ይልቅ ከሌላው ሰው መስማት ቀላል ስለሆነ ወይስ የጊዜ ቁጠባ?

 ዘመኑ አብዛኛውን የሰው ልጅ ወደ ዘመናዊው ቴክኖሎጂ ወለድ ወደሆነው የኢንተርኔት እይታ ወደማተኮር ካሸጋገረው ከረምረም ብሏል። በእርግጥም ይኽ የኢንተርኔት ዘመን ከጊዜ ቁጠባ ባለፈ በከፍተኛ ጥናት የተደረሰባቸውን መረጃዎች በአንድ መስኮት ስር አቀናጅቶ በማቅረብ በኩል ወደር የማይገኝለት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፣ በማድረግም ላይ ይገኛል። እንዲህም ሆኖ በዚህ የዌብሣይት ድረጎፆች ላይ ያሉት ቁም ነገሮች እንደተጠበቁ ሆነው ለቁጥር ያስቸገሩ ሀሰተኛ መረጃዎችና አሉባልታዎች እንደሚገኙበትም ከማንም የተሰወረ አይሆንም።

 በዚህ መልእክቴ ላይ እንኳን ማቅረብ የፈለኩት የኛው ጉድ ስለሆነው እና ሥር እየሰደደ ስለመጣው ሳያዩ እና ሳያረጋግጡ ሀሰተኛ ወሬ ማባዛት እና ማዛመት ስለሚወዱ ግለሰቦች ነው። የኢንተርኔቱንም የሀሜትና የሃሰት መረጃዎች በተመለከት የምለውም አላጣም። (…Continued)

Read Full Editorial

የትውልድ አሳፋሪነት በአባቶች ኩራት ሲሸፈን

ውድ አንባቢዎቻችን ‹‹እንኳን ለኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ›› ለአዲሱም የኛ ዘመን አንባቢዎቻችንን ባቅማችን ያገኘነውን ለማካፈል ከዚህም ከዚያም ብለን በተለያዩ አምዶቻችን ያካተትናቸውን ይዘን ብቅ ብለናል፡፡ አንብቦ ከመረዳትና ከማወቅ ይልቅ ማውራት ሳይቀናን አልቀረም ብትሉኝም መልሴ አልተሳሳታችሁም ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህቺ ነገ ለምታልፍ ዓለም ባውቅ ባላውቅ ለኔ ምን ይጠቅመኛል፤ ለዛሬ በልቼና የምፈልገውን አድርጌ ካደርኩ የነገው ለኔ ምኔ ነው የምንል በቁጥር እየበዛን የመጣን ይመስለኛል፡፡ አውርተነውና ተርከነው ግዜያዊ እርካታ ከፈጠረልን ለእውነትነቱ ወይም የተዛባ ለመሆኑ ግድም አይሰጠን፡፡

ጥንት አያቶቻችን የፈፀሙትን ጀግንነት እየተረክን እነሱ ለሃገራቸው የሰሩትን መልካም

ሥራና ጀብዱ እኛ የፈጸምነው ይመስል መኩራራትና እነሱን እንደምሳሌ በመጥቀስ ተረት፤ ተረት ማውራት ከጀመርን ዓመታት አስቆጠርን፡፡ አያቶቻችን ለሃገራቸው በሰሩት መልካም ስራ ላይ የጨመርነው ነገር ሳይኖር በጀግንነት ካቆዩት የቀነስነው፤ ካወረሱን ድንቅ ታሪክ የሚያሳፍር ቀለም የቀባነው እየበዛ የመጣ ይመስላል፡፡ ደግሞ እኮ አውርተን ያለማባራታችን እና አለማፈራችን ነው የሚደንቀው፡፡

ከጥንቶቹ አያቶች የጀግንነት ሥራቸውን በሥም እየጠቀስን ‹‹እገሌ የተባለው መሪያችን እንዲህ አድርጎ…ጠላትን አሳፍሮ..፤ እንትና የተባለው ንጉሳችን በጀግንነት ሥራው ዓለም ያደነቀው ነበር›› እያልን በጠረጴዛ ዙሪያና በአደባባይ ከማውራት አልፈን ለሌሎችም ታሪካችንን ለማያውቁ መተረክ ጀምረናል፡፡ በአያቶቻችን መልካም ታሪክ ላይ የጨመርነው አዲስ ነገር የለም፡፡ ድንገት ከእነሱ በኋላ የሰራነው (…Continued)

Read Full Editorial

መስማት እንጂ ማየት የተሳናቸው

የሰው ልጅ እንደተፈጥሮው እና እንደ ልምዱ አንድን ነገር የመቀበል ባሕሪዩም ይለያያል። አንዳንዱ ከሰው የሰማውን ነገር ለሌላ ሰው ከመንገሩ በፊት የነገሩን ትክክለኛነት ማጣራት ሲፈልግ፣ ከፊሉ ደግሞ የሰማውን ነገር ሳይጨምርና ሳይቀንስ ለሌላው ማውራት ይወዳል። ከዚህ ባለፈ ደግሞ የሰማውን ነገር ቆርጦ እና ቀጥሎ ለእሱ በሚያመቸው መንገድ ላገኘው ሁሉ የሚያቀብል አለ። ቆርጦ ቀጥል የሚሉት ዓይነት።

ለምን ይሆን ሰዎች ከማየት ይልቅ መስማት የሚቀናቸው? ለማንበብ ወይም በቦታው ከመገኘት ይልቅ ከሌላው ሰው መስማት ቀላል ስለሆነ ወይስ የጊዜ ቁጠባ?

ዘመኑ አብዛኛውን የሰው ልጅ ወደ ዘመናዊው ቴክኖሎጂ ወለድ ወደሆነው የኢንተርኔት እይታ ወደማተኮር ካሸጋገረው ከረምረም ብሏል። በእርግጥም ይኽ የኢንተርኔት ዘመን ከጊዜ ቁጠባ ባለፈ በከፍተኛ ጥናት የተደረሰባቸውን መረጃዎች በአንድ መስኮት ስር አቀናጅቶ በማቅረብ በኩል ወደር የማይገኝለት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፣ በማድረግም ላይ ይገኛል። እንዲህም ሆኖ በዚህ የዌብሣይት ድረጎፆች ላይ ያሉት ቁም ነገሮች እንደተጠበቁ ሆነው ለቁጥር ያስቸገሩ ሀሰተኛ መረጃዎችና አሉባልታዎች እንደሚገኙበትም ከማንም የተሰወረ አይሆንም።

በዚህ መልእክቴ ላይ እንኳን ማቅረብ የፈለኩት የኛው ጉድ ስለሆነው እና ሥር እየሰደደ ስለመጣው ሳያዩ እና ሳያረጋግጡ ሀሰተኛ ወሬ ማባዛት እና ማዛመት ስለሚወዱ ግለሰቦች ነው። የኢንተርኔቱንም የሀሜትና የሃሰት መረጃዎች በተመለከት የምለውም አላጣም። (…Continued)

Read Full Editorial

ጁሓራዊ በረከት

Scroll To Top